Tuesday, April 23, 2013

የሐዘን ጥሪ



የሰዉ ልጅ በምድር በሚኖርበት ዕድሜዉ ደስታንና ሐዘን እየተፈራረቁበት መኖሩ ግድ ነዉ፤ሆኖም ግን ለአንዳንዱ ደስታዉ ሲበዛለት(የደስታ መግለጫ ሲጎርፍለት፣ ደስታ ሲያሰቃየዉ፣ ደስታ ሲያማርጥ፣በደስታ ነፍሱ ስትሰቃይ…) ለሌላኛዉ ወገን ደግሞ ሐዘን ይደራረብበታል(ተስፋዉን ያጨልምበታል፣ ያለዉን ደስታ ይነጥቀዋል፣ …) ደስታን እንደማንኛዉም ሰዉ ብዙ ጊዜ እንደማጨዴ የዝያኑ ያህል ደግሞ ሐዘንን ቃርሜአለሁ ከሌላኛዉ ቀን በተለየ ዛሬ አዘንኩና አንድ ነገር ትዝ አለኝ፡-ሰዉ ሲደሰት ደስታዉን ለሚወዱትና ለሚወዳቸዉ ለማካፈል ሲሻ እንዲህ በማለት የደስታዉን ተካፋዮች ወደ ደስታዉ አዉድማ ይጋብዛል፡፡
“የማክበር ሰላምታዬን እያቀረብኩ … … ብሎ ይጀምርና የደስታዉን መነሻ ጠቅሶ … ይህን በማስመልከት ባዘጋጀሁት … በማለት ያስከትልና ጥሪዉን እንዲህ በማለት ያስተላልፋል ( እንደ አስፋላጊነቱ ) … የደስታዬ ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ በማክበር ጠርቼዎታለሁ፡፡ (ጠሪ አክባሪ ሳይሆን) ጠሪዉ ደስ ያለዉ ስዉ ነዉ፡፡”
ወገኔ፡- ደስ ያለዉ እንዲህ ብሎ ቃላት ከሽኖ ከጠራ በሐዘን ልቡ የተሰበረ ሰዉ ሐዘኑን ይጋሩት (ይካፈሉት) ዘንድ ዘመድ ወገኖቹን እንዴት ብሎ(እያለ) ይጥራ? እንዴትስ ብሎ ሐዘኑን ያጋራ? ግራ ስለገባኝ ንገሩኝ፡፡  

No comments:

Post a Comment